Fana: At a Speed of Life!

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከአሸባሪው ህወሓት ዘረፋ በተረፈው ንብረት እንኳን መስራት እንዳይችል ሆኖ ወድሟል- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላይ ከፈጸመው ዝርፊያ በተጨማሪ በቀረው ንብረቱ እንኳን ስራ እንዳይጀምር አድርጎ አውድሞታል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ ያደረሰበትን የወልድያ ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተዋል።
ወራሪው የህወሓት የሽብር ቡድኑ የዘረፈውን የዩኒቨርሲቲውን ንብረት ጭኖ ሲወስድ መውሰድ ያልቻለውን አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎ አውድሞታል።
አቶ ገዱ የዩኒቨርሲቲው ውድመት የሽብር ቡድኑ አባላት መንግስትን ወይንም ፖለቲከኞችን ሳይሆን ሕዝብን አምርረው የሚጠሉ፤ ሕዝብና የሕዝብ የሆነን ሁሉ ከማጥፋት የማይመለሱ መሆናቸውን ያሳየ ነው ብለዋል።
አሸባሪው ቡድን ወልዲያ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በደረሰበት ሁሉ የፈጸመው ውድመትና ዝርፊያ ቆሜለታለሁ የሚለው የትግራይ ሕዝብም ሲያፍርበት የሚኖር ጥፋት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በዚህ ደረጃ በሕዝብ ላይ የከፋ ጥላቻ ከተጠናወተው የሽብር ቡድኑ ተግባር ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ ይገባል ያሉት አቶ ገዱ፥ ዩኒቨርሲቲውም ከቀደመው በተሻለ ሁኔታ መልሶ ይገነባል ብለዋል።
የሰሜን፣ የደቡብ ወሎ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስም ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ውድመት ይኖራል፤ ነገር ግን በዩኒቨርሲቲው ላይ የደረሰው ተምሬያለሁ ከሚል አካል የማይጠበቅ ነው ብለዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ተግባር ምንም ግብ የሌለው ነው ያሉት ብጹዕነታቸው ይህንን ውድመትና ጥፋት አዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መጥተው በዓይናቸው ቢመለከቱ ሚዛናዊ ፍርድ መስጠት ያስችላል ብለዋል።
“የትግራይ እናት ላከችን” ያለው የጥፋት ሃይል የፈጸመው ድርጊት “እውነት የትግራይ እናቶች ፍላጎት ነው ወይ” ሲሉም ነው የጠየቁት።
ያለፉት ወራት አሸባሪው ህወሓት ካደረሰብን ጉዳት በላይ እስላም ክርስቲያኑ በአንድነት የቆምንበት፣ ለቀጣይም ትምህርት ያገኘንባቸው ነበሩ ያሉት ደግሞ የወልድያ ከተማ የሠላም ኮሚቴ አባል ሃጂ ያሲን እድሪስ ናቸው።
ሃጂ ያሲን የሽብር ቡድኑን ወራሪዎች የፈጸሙት ክፋት፣ ዝርፊያና ውድመት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ነው ብለዋል።
አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ላይ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ውድመት እንዳደረሰበት ኢዚአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.