ቢዝነስ

በ5 ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርት የወጪ ንግድ 203 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

By Feven Bishaw

December 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያው 5 ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርት የወጪ ንግድ 203 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ5 ወራት ውስጥ ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርት 215 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነው 203 ሚልየን ዶላር ወይም የእቅዱን 94 በመቶ ማግኘት የተቻለው፡፡