Fana: At a Speed of Life!

ሀዋሳ ላይ ሲደረግ የነበረው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዘጠኝ የጨዋታ ሳምንታትን ያስተናገደው የሃዋሳ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታዎች ባህር ዳር ከነማ ከአዳማ ከነማ ጋር 9፡00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የቀድሞው የባህር ዳር ከነማ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ አዳማን ይዞ ባህር ዳርን ወደ ሚገጥምበት ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ መሪ ከሆነው ፋሲል ከነማ ጋር ያለቸዉን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል።
አዳማ በበኩሉ ካለበት የውጤት ቀዉስ ለመውጣት እና ደረጃዎችን ለማሻሻል ጨዋታዉን የሚያደርግ ይሆናል ፡፡
በባህር ዳር ከነማ በኩል ቀድመው ጉዳት ላይ ከቆዩት በተጨማሪ ሁሴን ማውሊ በዛሬው ጨዋታ እንደማይሰለፍ የታወቀ ሲሆን፥ ሌሎች ተጫዋቾች ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል ፡፡
በአዳማ ከነማ በኩል የተሰማ የጉዳት ዜና አለመኖሩን ሶከር ኢትዮጵያ በዘገባዉ አስታወቋል፡፡
በሌላ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.