Fana: At a Speed of Life!

2 ሺህ ያህል ሰዎች በነጻ ትራንስፖርት ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል- ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚ/ር

አዲስ አበባ፣ ታሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በላምበረት መናኸሪያ እየተሰጠ ያለውን ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሯ ዛሬ ሌሊት ላምበረት መናኸሪያ በመገኘት እየተሰጠ ያለውን የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት በጎበኙበት ወቅት፥ የልዩ ባሶች የጋራ ኮሚቴ ከታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ 30 አውቶብሶችን በማሰማራት እስከ 2 ሺህ ያህል ሰዎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገልፀዋል።
ከደሴና ወልድያ በተጨማሪ ወደ ባህርዳር ከተማ ለመሄድ ጥያቄ እየቀረበ ስለሆነ በቀጣይ ይህን ጥያቄ ለመመለስ መታቀዱንም አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትሯ የትራንስፖርት ዘርፍ ተዋንያን ይህን እና ሌሎች ትልቅ ማህበራዊ ኃላፊነትን ሀገር በፈለገችበት ወሳኝ ወቅት በመወጣታቸው አመስግነዋል።
ለተመላሾችም እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.