Fana: At a Speed of Life!

በ2 ቢሊየን ብር እየተገነባ ያለው የድሬዳዋ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ግንባታ 95 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ግንባታ 95 በመቶ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ባህር ትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት አስታወቀ፡፡
ፕሮጀክቱ ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን በመጪው ጥር ወር ላይ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል።
ተርሚናሉ ከባቡር መስመር እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ፓርክ እና ከአውሮፕላን ማረፊያ በቅርብ ርቀት ላይ የተገነባ መሆኑን ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወደቡ ከሞጆ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ቀጥሎ የባቡር መሰረተ ልማት ያለው ሁለተኛው ደረቅ ወደብና ተርሚናል ሲሆን በ34 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ ነው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.