Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በሽብር ቡድኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን የመመለስና የመደገፍ ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽብር ቡድኑ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስና የመደገፍ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ።
የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም በአሸባሪው ቡድን የተጎዱ ዜጎችን ምላሽ ለመስጠት የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማእከል በማቋቋም ተገቢው ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ኮሚሽኑ በመጀመሪያ ደረጃ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመቀበል ሰብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንም ጠቅሰው፥ የምግብ፣ ነጻ የጤና አገልግሎትና ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል ነው ያሉት።
እስካሁን 160 ሺህ 151 ተፈናቃዮች ድጋፍ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውንም ገልጸዋል።
በርካታ ተፈናቃዮች በራሳቸው ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ ከመጪው የልደት በዓል በፊት ቀሪ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ ብለዋል።
ቀሪ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የግል የትራንስፖርት ድርጅቶች አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ከጠላት ነፃ በወጡ አካባቢዎች ምግብ የማስገባት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን ከ70 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ጠላት ወረራ በፈጸመበት አካባቢ ሙሉ በሙሉ ውድመት በመፈጸሙ ነፃ በወጡ አካባቢዎች በወር 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል እህል ለ11 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕዝብ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ ሀገራዊ ንቅናቄ እንዲፈጠር በማድረግ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችና የግለሰቦች ቤቶች ወደ ነበሩበት የመመለስ ተግባር ይፈጽማል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.