Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በምትፈልገው ሁሉ አለንልሽ በማለት ጥሪዋን ተቀብለን መጥተናል – ትውልደ ኢትዮጵያውያን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በምትፈልገው ሁሉ አለንልሽ በማለት መጥተናል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ዳያስፖራዎች ተናገሩ፡፡
ጥሪውን ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዳያስፖራዎች ወደ አገር ቤት እየገቡ ነው፡፡
በውጭ አገራት የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ስለ አገራቸው በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበር ገልጸው÷ አሁን ደግሞ አገሪቷ በምትፈልገው ሁሉ ለማገዝ በአካል እንደተገኙ ለኢዜአ አስረድተዋል፡፡
አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስለ ኢትዮጵያ ሲዘግቡ ፍጹም ሰላም እንደሌለ አድርገው መሆኑን ጠቁመው÷ በአካል በኢትዮጵያ ተገኝተው የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን ማረጋገጥ መቻላቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
አሸባሪው ህወሓት በቀሰቀሰው ጦርነት የተጎዳው ኢኮኖሚ እንዲያገግም በተግባር ድጋፍ እንደሚያከናውኑም ገልጸዋል።
እንደአቅማቸው የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር ይዞ በመግባት አገር ከእነርሱ የምትጠብቀውን ሁሉ ለማድረግ እንደመጡም ነው የገለጹት።
”ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለአገሩ ክብር በግንባር ሲዋደቅ እኛ ደግሞ አገር ስትጠራን ትኬት ቆርጦ መምጣት ምንም ማለት አይደለም” በማለት መምጣት ከነበረባቸው ጊዜ አስቀድመው አገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ስለመምጣታቸው ጠቅሰዋል።
በውጭ አገራት የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ምዕራባውያኑ ኃያላን አገራት በውስጥ ጉዳይ በመግባት በአገር ላይ እያደረጉ ያለውን ጫና አደባባይ ወጥቶ የበቃ ንቅናቄን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.