Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ዘርፍ ጠንካራ ክትትልና ግምገማ እንደሚያስፈልገው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኮኖሚ ዕድገቱ በተሻለ ምዕራፍ እንዲገኝ ያግዛል ተብሎ የሚጠበቀው የትምህርት ዘርፍ ጠንካራ ክትትልና ግምገማ እንደሚያስፈልገው የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር በሚያካሂደው የመንግስት ተቋማት የ100 ቀን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የ100 ቀን ዕቅድ ትግበራ ላይ ግምገማ ተካሄዷል።
የትምህርት ሚኒስቴር ላይ በተካሄደው ግምገማ ገምጋሚ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎች ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምላሽ ሰጥተዋል።
ግምገማው የኢኮኖሚ ዕድገቱ በተሻለ ምዕራፍ እንዲገኝ ያግዛል ተብሎ ለሚጠበቀው የትምህርት ዘርፍ ጠንካራ ክትትልና ግምገማ እንደሚያስፈልገው ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
አያይዘውም ግምገማው ተቋማትን የምንቆጣጠርበትና የምናስተዳድርበት ዋነኛው ሥርዓት ክትትልና ግምገማ እንደሆነ መናገራቸውን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.