Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከህወሃት ወረራ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች በየወሩ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል እህል ያስፈልጋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአማራ ክልል አሸባሪው ህወሓት በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በየወሩ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የምግብ እህል እንደሚያስፈልግ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽነሩ አቶ ዘላለም ልጃለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ አሸባሪው ህወሓት በክልሉ በወረራ ይዟቸው በቆዩ ሰባት ዞኖች ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል።

የገና እና የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ አገር ቤት የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወገኖችን በማወያየትና በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች እንዲመለከቱ በማድረግ በመልሶ ማቋቋም ሥራ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በወረራ ተይዘው በቆዩ አካባቢዎች ለሚኖሩ 11 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች በአሁኑ ወቅት በየወሩ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የምግብ እህል ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ የሽብር ቡድኑ ለአምስት ወራት በወረራ ሲቆይ ቀዬአቸውን ያልለቀቁ 9 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች በስቃይ ውስጥ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

እነዚሁ ዜጎች ምንም አይነት የእርዳታ እህል ድጋፍ ከአንድም ዓለም አቀፍ ድርጅት ባለማግኘታቸው ለከፋ ርሃብ ተዳርገው እንደቆዩ ተናግረዋል።

ወደ ቀዬአቸው እየተመለሱ ለሚገኙም ሆነ አካባቢያቸውን ሳይለቁ ለቆዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአሁኑ ወቅት ከ70 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል እየተከፋፋለ መሆኑን ኮሚሽነሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ህብረተሰቡ፣ ባለሀብቱና መላው የኢትዮጵያ ህዝብና ወዳጆች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ዘላለም ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሚሽኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በጀመረው ሥራ እስካሁን ድረስ ከ313 ሺህ በላይ ዜጎች መመለሳቸው ይታወሳል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.