ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ካሜሩን ለሚያደርገው ጉዞ የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

December 25, 2021

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ካሜሩን ለሚያደርገው ጉዞ በስካይ ላይት ሆቴል የተሰናዳው የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

ዋልያዎቹ በሀገር ባህል ልብስ አሸብርቀው በስፍራው የተገኙ ሲሆን፥ የመንግሥት ባለስልጣናት ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ መታደማቸዉን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።