Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የደሴ ፋና ኤፍ ኤም ጥገና ተደርጎለት ወደ ስርጭት ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በቅርቡ በአሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የደሴ ፋና ኤፍ ኤም ጥገና ተደርጎለት ወደ ስርጭት ተመልሷል፡፡

አሸባሪው ቡድን ደሴን በወረረበት ወቅት በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እንደተናገሩት፥ ማሰራጫ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደመ ሲሆን÷ በገንዘብ ወደ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት የቴክኒክ ንብረት ወድሟል ፡፡

የደሴ ፋና ኤፍ ኤም በዋነኛነት የህብረተሰቡን ኑሮ ሊለውጡ የሚችሉ ባህል፣ ታሪክ ፣ቋንቋ የህዝቦች ትስስርን እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የሚያደርጉ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የማይወደው አሸባሪው ቡድን ማሰራጫውን በማውደም የህዝብ ጠላትነቱን አስመስክሯል ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ ውድመቱ ከፍተኛ ቢሆንም ለአካባቢው ህብረተሰብ መረጃ ለማድረስ እና ማህበረሰቡ የደረሰበትን የስነ ልቦ ጉዳት ለመጠገን ብሎም በመልሶ ግንባታው አስተዋፅኦ ለማድረግ በአዲስ መልክ የሚያስፈልጉ መሳርያዎችን በመግዛት ስርጭቱ እንዲጀመር ተደርጓል ብለዋል፡፡

ለዚህም በመጀመርያ ዙር ለስርጭት ማስጀመርያ 5 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎል፡፡

ስርጭቱ በፍጥነት እንዲጀመር መደረጉም ፋና የህዝብ መሆኑን እና የአሸባሪውን ቡድን አስነዋሪ ድርጊት እና ህብረተሰቡ የደረሰበትን በደል ለማሳየት ታልሞ ነው ብለዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.