Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማና አካባቢውን ሰላም አስተማማኝ ማድረግ የክልሉና የሀገርን ሰላም የማስጠበቅ መሰረት ነው -አቶ አገኘሁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማና አካባቢውን ሰላም አስተማማኝ ማድረግ የክልሉና የሀገርን ሰላም የማስጠበቅ መሰረት ነው አሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፡፡
 
የህልውና ዘመቻውን መሰረት አድርጎ የጎንደር ሰላምና የእድገት ማህበር ያዘጋጀው የጎንደር የሰላምና እድገት ጉባኤ፡፡
 
በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤው አቶ አገኘሁ ተሻገር፥ ጉባኤው አሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን በወገን ጥምር ጦር ሽንፈት በተከናነበበት ወቅት የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
 
የጎንደር ህዝብ አሰፍስፎ የመጣውን የህወሓት ወራሪ ሃይል አንድ ሁኖ በመመከት ታሪካዊ ጀብድ ፈፅሟል ነው ያሉት አፈ ጉባኤው ፡፡
 
የሽብር ቡድኑ ህወሓት ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተደመሰሰ ድረስ የጎንደር ህዝብ ስጋት ውስጥ መሆኑን ጠቁመው፥ በተሻለ መደራጀት አካባቢውን ከጠላት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
 
ትግሉ ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም፤ የተደራጁ ጥቂቶች ያልተደራጁ ብዙዎችን ያሸንፋሉና ህዝቡና ማህበራት በጋራ በመደራጀት ለሀገር ሰላም መጠበቅ መስራት አለባቸው ብለዋል።
 
ጎንደርና አካባቢው ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም እንዳለው ጠቁመው፥ በቅርቡ ከውጭ የሚመጡ ዳያስፖራዎች ባለው ምቹ እድል በመጠቀም የሽብር ቡድኑ ያደረሰውን የኢኮኖሚ ወድቀት መመለስ አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
በጉባኤው ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
 
በምናለ አየነው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.