Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ካለችበት ችግር ለማውጣት ወጣቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል-አቶ ታዬ ደንደአ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ካለችበት ችግር ለማውጣት ወጣቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታየ ደንደአ ገለጹ፡፡
 
ሶስተኛው ዙር የሰላም ሚኒስቴር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ፥ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም እና እድገት ለማረጋገጥ ወጣቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን ካለችበት ችግር ለማውጣትም ወጣቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፡፡
 
ይህ ተሞክሮም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ እና በቅንጀት መስራት እንደሚገባ ነው የጠቆሙት ፡፡
 
 
እስካሁን ድረስ በዘርፉ ከ17 ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን፥ አሁን ላይም ለ3ኛ ዙር መሰጠት መጀመሩ ተገልጿል።
 
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ሰላሟን ታረጋግጣለች ያሉት አቶ ታዬ፥ ወጣቶች አንድነታቸውን በማጠናከር በአብሮነት መጓዝ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
 
በአብዱረህማን መሀመድ
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.