በውይይት ጠቀሜታ እና አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ችግራችንን በውይይት መፍታት ለምን ተሳነን? በሚል ርዕስ የምክክር መድረክ በሂልተን ሆቴል ተካሄደ።
በምክክር መድረኩ ውይይት በሀገር ግንባታ ባለው አስተዋፅኦ፣ እውነተኛ ውይይት ወደ ዴሞክራሲና ስልጡን ፖለቲካ እንዴት እንደሚያሻግር እንዲሁም በሂደት ውስጥ የሚመጣ ውጤታማ ንግግርን በተመለከተ ተሳታፊዎች ተወያይተዋል።
ከዚህ ባለፈም ከመፈረጅ ነፃ በሆነና በእምነት ላይ የተመሠረተ ውይይት ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ምክክር አድርገዋል።
መድረኩን ፍትህ ለሁሉም ከአዕላፍ መልቲ ሚዲያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን፥ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሰላም ሚኒስቴር ተወካዮች እና ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ላይ ሁሉንም ያሳተፈ እውነተኛ ውይይትን ማጎልበት በሁሉም ዘርፍ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት እንደሚያስችል ተገልጿል።
እውነተኛ ውይይት ክርክር፣ የራስን ሀሳብ በሌሎች ላይ አለመጫን፣ አሳታፊ እና የጋራ ግብ ያለው የንግግር ሂደት መሆኑም ነው የተገለጸው።
በመታገስ አየልኝ እና ማርታ ጌታቸው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision