Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ጋትራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ጋትራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 16 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።

አደጋው ዛሬ 6 ሰዓት አካባቢ የደረሰ ሲሆን፥ ፍሬን እንቢ ያለው ተሽከርካሪ ገበያ መሃል ገብቶ የ50 ዓመት እናት ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

የሰጠማ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር እስማኤል እርገጤ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደ ተናገሩት ፥ ህይወታቸው ካለፈው እናት በተጨማሪም አስር ሰዎች ላይ ከባድና ዘጠኝ ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በጋትራና በአጋሮ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ኢንስፔክተር እስማኤል ተናግረዋል።

አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ ለጊዜው መሰወሩንና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው ገልፀዋል።

በሙክታር ጠሃ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.