Fana: At a Speed of Life!

የእሁድ ገበያ በከተማዋ ዉጤታማ በሆነ መንገድ ቀጥሏል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ሳምንት 14ኛዉን የእሁድ ገበያ የመሸጫ ማዕከል እንደሚከፈት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የእሁድ ገበያ በከተማዋ ዉጤታማ በሆነ መንገድ መቀጠሉን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ከተጀመረ ከ 9 ሳምንታት በላይ የሆነዉ የእሁድ ገበያ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት በከተማችን ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል እንዲያግዝ ጤናማ የግብይት ስርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የግብርና ምርቶች በተለይም አትክልት፣ ጥራጥሬና የመኸር ሰብል ምርቶች ፣ የፋብሪካ ምርቶች በተሻለ አቅርቦትና በተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለሸማቾች እየቀረበ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በገበያ ተደራሽነትም በተለያዩ የከተማችን አካባቢዎች እየተስፋፋ 13 የደረሰ ሲሆን ÷ በቀጣይ ሳምንት 14ኛዉን የእሁድ ገበያ የመሸጫ ማዕከል እንደሚከፈት ገለጹ ።

የእሁድ ገበያ በታለመለት መንገድ እንዲሄድና ዉጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ገበሬዎች ፣ አምራቾች ፣ የኦሮሚያ እና የአዲስ አበባ የህብረት ስራ ማህበራት ፣ ደንብ አስከባሪዎች፣ አመራሮችና ባለሙያዎችን አመስግነዋል ።

የከተማዉ አስተዳደር በቀጣይም አምራቹ እና ሸማቹ በቀጥታ የሚገበያዩበትን ጤናማ የንግድ ስርዓት ለመፍጠር የጀመርናቸውን መሰል ተግባራት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል ከንቲባዋ ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.