Fana: At a Speed of Life!

ከተከፈቱ ህገወጥ የገንዘብ መላኪያ ድረ-ገፆች ሰዎች እንዲጠነቀቁ ባንኩ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ አጭበርባሪዎች የተሻለ የመዘርዘሪያ እና የመላኪያ ዋጋ እናቀርባለን በማለት መተግበሪያዎችን እየሰሩ ድረ-ገፅ ላይ እየለቀቁ በመሆኑ ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳሰበ፡፡

በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚላክን ገንዘብ ህጋዊ ለማድረግና የተበታተነ የገንዘብ አላላክን በአንድ ቋት ለመድረግ እንዲቻል http://xn--www-86o.eyezonethiopia.com/ አማካኝነት በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ይታወቃል።

ሆኖም አንዳንድ አጭበርባሪዎች ‘የተሻለ የመዘርዘሪያ እና የመላኪያ ዋጋ እናቀርባለን’ በማለት መተግበሪያዎችን እየሰሩ ድረ-ገፅ ላይ እየለቀቁ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ሲል ባንኩ አሳስቧል፡፡

እንዲህ አይነቱ የማጭበርበር ስራ ዳያስፖራው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ ለማስተጓጎልና ለአገር የሚጠቅመውን የውጭ ምንዛሬ ወደራሳቸው አገር በማስቀረትና ህጋዊ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውርን አገር ውስጥ በማስፋፋት አገርን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን መገንዘቡን ባንኩ ገልጿል።

እነዚህ አካላት በተለይ በቅርቡ ወደ አገራቸው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ኢላማ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው ያለው ባንኩ፥ ህጋዊ ያልሆኑ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማትን ባለመጠቀም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዲከላከሉ ባንኩ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ከ5 ዶላር ጀምሮ የ eyezonethiopia.com ድረ-ገጽን በመጠቀም ድጋፋችውን እንዲያደርጉ መጠየቁን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.