Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ከፓርቲዎች ጋር እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በፓለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ አቤቱታዎች ዙሪያ ከፓርቲዎች ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡

በቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ በሚመራው በዚሁ ምክክር የፓለቲካ ፓርቲዎች በአባል እና አመራሮቻችን ላይ እንግልት እና እስር እየደረሰ ነው ሲሉ ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች አጣሪ ቡድን በዝርዝር እየተመለከተ ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቀረቡትን አቤቱታዎች መነሻ በማድረግ ከፓርቲዎች፣ ከገዢው ፓርቲ እና ከቦርዱ የተወከሉ አጣሪ ቡድን በመላክ እና በማጣራት ሂደት ላይ ያሉ መልካም እና መስተካካል ያለባቸውን ጉዳዮች ተመልክተዋል።

በውይይቱ የብልፅግና ፓርቲ ተወካይና የፓርቲው የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ አቶ ዛዲግ አብረሃ አቤቱታዎቹን በጥልቀት ለመመልከት በስራ አስፈፃሚ ደረጃ የሰው ሃይል ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ፓርቲዎችም ቦርዱ ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት አድንቀው ለምላሹ ግን ጠንካራ ስራ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ አሉ ያሏቸውን ክፍተቶችንም አንስተዋል።

በተጨማሪም ቦርዱ ከመንግስት የሚሰጠውን ድጋፍ ለመወሰን ተሻሻሽሎ የወጣ መመሪያ ላይም እየተወያየ ነው።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.