Fana: At a Speed of Life!

ከ95ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ95 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገ ክትትል 43 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 51 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ÷ በቅደም ተከተላቸው 13 ነጥብ 9 ሚሊየን፣ 11 ነጥብ 8 ሚሊየን እና 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ይዘዋል ነው የተባለው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ መሆናቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ወርቅ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገራ ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝብ ምስጋና አቅርቧል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ÷ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቀርቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.