Fana: At a Speed of Life!

ወደ ሀገር ቤት የሚጓዙ የዳያስፖራ አባላትን የሚያስተናግድ ድረገፅ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ መሰረት ወደ የኢትዮጵያ የሚጓዙ የዳያስፖራ አባላትን የሚያስተናግድ ድረገፅ ይፋ መሆኑን የዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
አንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ÷ በርካታ የዳያስፖራ አባላት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረትም ጉዳዩን እንዲያስተባብር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ሴክሬታሪያትና አስተባባሪ የሆነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ÷ የዳያስፖራውን የቆይታ ጊዜ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ እንዲሁም ለዳያስፖራው ሁለገብ መረጃ የሚያቀርብና የዳያስፖራ አባላትን መረጃዎች ለማሰባሰብና ለማደራጀት የሚያስችል ወጥ የሆነ የኦንላይን የመረጃ ድረ-ገጽ ይፋ አድርጓል፡፡
የድረ-ገጹ አድራሻም www.greatethiopianhomecoming.org ነው፡፡
የዳያስፖራ አባላት በድረ-ገጹ register በሚለው ታብ በመግባት በሚያገኙት ፎርም እንዲመዘገቡ እየጠየቅን፤ ከድረ-ገጹ መረጃዎችን ማየትና ያሏቸውን ጥያቄዎች በመጻፍ ቀጥተኛ ምላሽ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን ሲል ኤጀንሲው በፌስክ ገጹ አሳውቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.