Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሃት በሴቶችና ህጻናት ላይ ያደረሰውን የስነ ልቦና ጉዳት ለማከም እየተሰራ ነው – የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 18፣2013 (ኤፍ ቢሲ) አሸባሪው ህወሃት በሴቶችና ህጻናት ላይ ያደረሰውን የስነ ልቦና ጉዳት ለማከም እየተሰራ መሆኑን በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ ተናገሩ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ከፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፥ አሸባሪው ህወሃት ከኢትዮጵውያን ባህል እና እምነት ባፈነገጠ መልኩ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሴቶችና ህጻናት ላይ የአስገድዶ መድፈር፣ ድብደባ እና ግድያ ወንጀሎችን ፈፅሟል፡፡
ሴቶችና ህጻናት የሚገለገሉባቸው ቁሳቁሶች በሽብር ቡድኑ ወድመዋል፤ ህጻናት ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተከትሎ የተለያዩ እንግልቶች ደርሶባቸዋል፤ በዚህም እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ ስነ ልቦናዊ ጉዳት መጋለጣቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀዋል፡፡
ስለሆነም የደረሰውን የስነ ልቦና ጉዳት ለመከላክል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በባለሙያዎች በመታገዝ የተለያዩ የስነ ልቦና ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም ከወረራ ነጻ በወጡ የአፋርና የአማራ ክልል አካባቢዎች መንግስት የወደሙ አግልግሎት ሰጪ ተቋማትን እያሰጀመረ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ሙና፥ ሴቶች እና ህጻናትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደ ጤና እና ትምህርት ቤት ያሉ መሰረተ ልማቶች ቅድሚያ ተስጥቷቸው እየተሰሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
አሁን ላይ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ 4 ሚለየን ሰዎች መኖራቸውን እና ከእነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ሴቶች ህጻናትና ታዳጊዎች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡
የወደፊት የሃገር እጣ ፈንታ የሚወሰነው በእነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች በመሆኑ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ህጻናት እና ሴቶችን ለማቋቋምና በስነ ልቦና ድጋፍ ለማደረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.