Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከር ትልቅ እድልና አማራጭ ገበያ መሆኑ መታወቅ አለበት-ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከር ትልቅ እድልና አማራጭ ገበያ እንደሆነ መታወቅ አለበት ሲሉ የ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ተናገሩ፡፡
 
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ100 ቀናት ዕቅድ ትግበራን ገምግሟል፡፡
 
በመድረኩ የፕላን ና ልማት ሚኒስትር ዶክተርፍጹም አሰፋ ፣ በፕላን ስታቲስቲክስ እና ፖሊሲ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ፣ የግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጥሩማር አባተ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
 
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ላይ በተካሄደው ግምገማ÷ ገምጋሚ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎች ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ምላሽ ሰጥተዋል።
 
የፕላን ና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በበኩላቸው ÷ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከር ትልቅ እድልና አማራጭ ገበያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የሁለትዮሽ ንግድ ግንኙነቶችና ድርድር ፣ የገቢ ምርቶች፣ የወጪ ምርቶች፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ተደራሽ ማድረግ፣ 17 ተቋማትን ያካተተ የገበያ ዋጋ ማረጋጋት እና የህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ላይ ጥሩ አፈፃፀም እየታየ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 
በቀጣይም የምርቶቻችን መዳረሻ ማስፋት ይኖርብናል ማለታቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.