Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አስራ አንዱ ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አስራ አንዱ ስራ መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በደሴና ኮምቦልቻ ያወደማቸውንና ጉዳት ያደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች መልሶ ለማቋቋም ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቦታው ላይ ጊዜያዊ ቢሮ ከፍቶ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው ተብሏል፡፡

ጊዜያዊ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት፣ ከባለሀብቶች፣ እንዲሁም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ባደረገው ቅንጅታዊ ስራ 11 የጨርቃጨርቅ፣ የምግብና መጠጥ እንዲሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ምርት የማምረት ስራ ጀምረዋል ነው የተባለው፡፡

በአካባቢው የሚገኙ ባንኮች፣ጉምሩክ፣ኢትዮ ቴሌኮም እና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ መጀመራቸው እና ፋብሪካዎቹ ወደ ስራ መግባታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ያሉት የጊዜያዊ ቢሮው ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በርጋ ናቸው፡፡

በቅርቡ ኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ሲለቀቅ ተጨማሪ ፋብሪካዎች ወደ ምርት እንደሚገቡ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.