Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የትምህርት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሓዊነት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የትምህርት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሓዊነት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡
 
በክልሉ ትምህርት ቢሮ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ከግል የትምህርት ተቋማት እና ሌሎች ድርጅቶች የተውጣጡ የትምህርት ዘርፍ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል ፡፡
 
የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አብድቃድር መሐመድ÷ ከለውጡ አንስቶ በክልሉ ትኩረት ተነፍጎት የነበረውን የትምህርት ዘርፍ የክልሉ መንግስት ከወትሮው በተለየ በጀቱን በእጥፍ ማሳደግ መቻሉን አንስተዋል ፡፡
 
ባለፍት ሶስት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎችን ያብራሩት ምክትል ሃላፊው፥ በዚህም በ93 ወረዳዎች የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ግንባታ፣ የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ልጆች ተጠቃሚ የሚያደርጉ 11 የአዳሪ ትምህርት ቤት የ1 ነጥብ 8 ሚሊየን የመፅሐፍት ስርጭት እና ከ8 ሺህ የሚጠጋ የመምህራን ቅጥር መፈጸሙን አንስተዋል፡፡
 
በተጨማሪም ለመምህራን ደሞዝ ጭማሪና ማስተካከያ መደረጉን አንስተው፥ ከዜሮ ክፍል እስከ ስምንተኛ ድረስ የክልሉን ባህልና ወግ እንዲሁም በትርጉም ወቅት የነበሩ የትርጉም መፋለሶችን ለማስቀረት በክልሉ ባለሙያዎች ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉን ጠቁመዋል፡፡
 
በአሸባሪው የህወሓት አገዛዝ ዘመን በክልሉ ጎሳዎች መሐል በሚፈጠር ግጭትና ፀብ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተዳክሞ ተማሪዎች በክፍል ተቀምጠው ያልተማሩት ትምህርት ፈተና ሰርቶ በመስጠት ትውልድን በዕውቀት የማቀጨጭ ስራዎች ተፅዕኖ ቀላል እንዳልነበርም አስታውሰዋል፡፡
 
ለትምህርት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሓዊነትም ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት እና ወላጆች በጋራ ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል መባሉን የሶማሌ መገናኛ ብዙሓን ዘግቧል፡፡
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.