Fana: At a Speed of Life!

በጣሊያንና ግሪክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቃዮች ከ120 ሺህ ዩሮ በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን እና ግሪክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሻባሪው የወያኔ ወራሪ ሀይል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 120 ሺህ 783 ዩሮ ድጋፍ አስረከቡ፡፡
አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች መቀጠላቸውን በጣሊያን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተያያዘ ዜና ዳያስፖራው ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተደረገለትን ጥሪ በመቀበል ወደ አገር ቤት መግባት ጀምሯል።
የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚሆን የአይነት ድጋፍ በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው ተብሏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.