Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ከተማ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁ መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት የሙከራ ትግበራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁ መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ይፋዊ ሙከራ ትግበራ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ተካሄደ።
እንደ ሀዋሳ ከተማ በአራት ትምህርት ቤቶች በ7ኛ ክፍል በሂሳብ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ተደርጓል፡፡
የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ በየነ በራሳ÷ በንግስት ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የመጽሐፍት ርክክብ አድርገዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ልጆች እውቀትን ብቻ ሳይሆን ክህሎትን ጭምር ይዘው የሚወጡበት በመሆኑ የትምህርቱ ዘርፍ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ በቴክኖሎጂ እውቀትና በሀገር በቀል የተዘጋጀ ትምህርት በ2015 ዓ.ም በሁሉም ትምህር ቤቶች በመደበኛ እነደሚጀመር መናገራቸውን ከሀዋሳ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ደስታ ዳንኤል÷ እንደ ሀገር የአሰራር ለውጥ ከሚያስፈልጋቸው አንዱ የትምህርት ዘርፍ በመሆኑ ስርዓተ ትምህርቱን በአዲስ ለመተካት የዝግጅት ስራው ተከናውኖ የሙከራ ትግበራው ይፋ ሆኗል ብለዋል።
የቀድሞው መጽሐፍ በይዘት የተጨናነቀ፣ ለማስተማር ምቹ ያልሆነ፣ አካባቢውን ታሳቢ ያላደረገና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.