Fana: At a Speed of Life!

የትራፊክ አደጋን መቀነስ የሚያስችል ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንገዶች ደህንነት ምክንያት የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚያስችል ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ግምገማው በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር ርዝመት ባላቸው መንገዶች ላይ ነው እየተካሄደ ያለው።

በግምገማው 500 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አደገኛ መንገድም ተለይቷል።

በሚኒስቴሩ የብሄራዊ መንገድ ደህንነት ፅህፈት ቤት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጥላሁን ገለታ እንዳሉት፥ በእነዚህ መንገዶች ላይ እንደየጉድለታቸው ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ለባለሙያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ግምገማው እና ስልጠናው ከስፔኑ ኤፕቲሳ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመሆን ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

በትእግስት አብርሃም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.