Fana: At a Speed of Life!

የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በቁልቢና ሀዋሳ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሺህዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮችና ጎብኚዎች በተገኙባቸው ቁልቢና ሀዋሳ በድምቀት ተከበረ ።
በበዓሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች እንዲሁም ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የመጡ ጎብኚዎች ተገኝተዋል፡፡
የንግስ በዓሉን በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ፈጣሪያቸውን በማመስገን አክብረዋል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ከሃይማኖታዊነቱ ባሻገር ለቁልቢ እና ሐዋሳ ከተሞች ድምቀትና የቱሪዝም መነቃቃት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተመላክቷል።
የዘንድሮው ክብረ-በዓል 1 ሚሊየን ዳያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ ተደርጎላቸው እየመጡ ባሉበት ጊዜ መከበሩም ለቱሪዝም እንቅስቃሴና ዕድገት ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ህዝበ ክርስቲያኑ በጸሎት እና በአንድነትን በሁሉም ዘርፍ የድርሻውን እንዲወጣ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቅርበዋል።
የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓልን በቁልቢ ያከበሩ ምዕመናን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየት የቁልቢ ገብርኤል ገዳምን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ከቱሪዝም ልማቱ ቤተክርስቲያኗን እና መንግስትን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በቁልቢና በአቅራቢያዋ በሚገኙ ከተሞች መሟላት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
ጥንታዊ የሆነው ገዳም በውስጡ የያዛቸው ቅርሶችም በተገቢው ሁኔታ መደራጀት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም እና በጥላሁን ይልማ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.