Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው እየገቡ ላሉ ዳያስፖራዎች ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ ነው – ጉምሩክ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ላሉ ዳያስፖራዎች ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመንደገኞች ጉዳይ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘራኤል ለአ÷ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ላሉ መንገደኞች የተለየ የጉምሩክ አገልግሎት መስጫ ቦታ በማዘጋጀት ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችን ይዘው የሚመጡ መንገደኞችም ያመጡትን ድጋፍ በቀላሉ ለማስረከብ እንዲያመቻቸው ከጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር መጋዘን በማዘጋጀት አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
 
የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ዓለም አቀፍ መንገደኞች ቡድን አስተባባሪ አቶ ዚያድ ኑረታ በበኩላቸው ÷ እንግዶችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር የ24 ሰዓት ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ዳያስፖራዎች ወደ ኢትዮጵያ ይዘው የመጡትን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች በህጋዊ መንገድ በመመንዘር ሀገራችን በቂ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ዳያስፖራዎች በተደረገላቸው መልካም አቀባበልና ፈጣን የጉምሩክ አገልግሎት መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
 

በቆይታቸው የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጤን እና መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ሰፊ የስራ እድልን ለመፍጠር እምዲሁም ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ በቂ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት እንደሚሰሩ መናገራቸውንከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.