Fana: At a Speed of Life!

ሶስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ምልምሎች ለስልጠና ወደ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ለመሰልጠን ወደ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ለገቡ በጎ ፈቃደኛ ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ተካሂዷል።

ፕሮግራሙ በሃይማኖት አባቶች እና በአገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተጀምሯል ።

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ይህ ወቅት ኢትዮጵያ ከራሷ አብራክ በወጡ ሃይሎች እና በወጭ ጠላቶች ጥምረት የተወጋችበት ወቅት መሆኑን ገልፀው ÷ ሆኖም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወጣቶች ህይወታቸውን ሰጥተው ኢትዮጵያን ታድገዋል ብለዋል ።

ኢትዮጵያ ከፍ የምትለው በህዝቦቿ ትብብርና ፅናት ነው ያሉት አቶ ብናልፍ ÷ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የኢትዮጵያን አንድነት እና ፍቅር ይበልጥ ልታጠነክሩ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በስልጠና እና በበጎ ስራ ቆይታቸው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀራረብ ኢትዮጵያን በደንብ የሚያውቁበት እና የኢትዮጵያውያን እውነተኛ ማንነት የሚረዱበት እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.