Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወደ አገር ቤት እየገቡ ለሚገኙ ዳያስፖራዎች ልዩ አቀባበልና መስተንግዶ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ አገር ቤት እንግባ ጥሪን ተቀብለው እየገቡ ለሚገኙ ዳያስፖራዎች ልዩ አቀባበልና መስተንግዶ እያደረገ መሆኑን ገለጸ።
ኢትዮጵያ የገጠማትን ወቅታዊ ፈተና በአሸናፊነት እንድትወጣ ዜጎች አንድ ላይ በመቆም ሀገርን ለማዳን እየተረባረቡ ይገኛሉ።
በተለይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቁርጥ ቀን ልጆች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅርና ጥብቅና አደባባይ በመውጣት አሳይተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው የሚመጡ ዳያስፖራዎችን በልዩ ሁኔታ ለመቀበል ሁለት ኮሚቴ በማዋቀር እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የግራውንድ ሰርቪስስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታደለ ባረጋ ለኢዜአ እንደገለጹ፣ የተቋቋሙት ኮሚቴዎች የደህንነትና የጸጥታ ጉዳዮችን ይከታተላሉ።
ወደ ሀገር ቤት ለመጡ ወገኖች የሚሰጠውን አገልግሎት በትኩረት የሚከታተሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ዳያስፖራዎቹ ችግር እንዳያጋጥማቸው ካጋጠማቸውም ኮሚቴው ወዲያው ተነጋግሮ እርምት በመውሰድ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል።
ዳያስፖራዎቹ የኢትዮጵያን ቆይታ አጠናቀው ወደሚኖሩበት ሀገር በሚመለሱበት ወቅትም አገልግሎቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ያለ እንከን እንደሚቀርብላቸው ጠቁመዋል።
አየር መንገዱ ከእነዚህ ዝግጅቶች በተጨማሪም ዳያስፖራው በረዥም ጊዜ ሀገሩን ናፍቆ ሲመጣ ደስ እንዲለው የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነውን የቡና ስነ-ስርዓት በመነሻቸውና በመዳረሻቸው ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.