Fana: At a Speed of Life!

ሐሰተኞች ከኢትዮጵያ ውጡ ሲሉ እውነቱን የሚያውቁት ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ ነው – ቢልለኔ ስዩም

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት ቢልለኔ ስዩም የ”ታላቁን ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ ላሉ ዳያስፖራዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ዓለም ከኢትዮጵያ ውጡ ሲል እውነቱን ያውቁ ለነበሩና ጥሪውን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ዳያስፖራዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው “ሐሰተኞች ከኢትዮጵያ ውጡ ሲሉ እውነቱን የሚያውቁት ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ ነው” ብለዋል።
አያይዘውም “ቤት በእርግጥም ልብ ያለበት ቦታ ነው” ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የ”ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” ማቅረባቸው ይታወሳል።
እስካሁን ጥሪውን የተቀበሉ ዳያስፖራዎች ወደ ሃገር ቤት እየገቡ ይገኛሉ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.