Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ግንባሮች የመከላከያ ሰራዊትን ላበረታቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ግንባሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ላበረታቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኝሁ ተሻገር ምስጋና አቀረቡ።

አፈጉባኤው በማይጠብሪ ግንባር በመገኘት አሸባሪውን የህወሃት ቡድን አይቀጡ ቅጣት የቀጡትን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት አበረታተዋል።

በታዋቂ አርቲስቶችና በፌዴራል ፖሊስ ማረሚያ ቤቶች የሙዚቃ እና የቲያትር ቡድን ቅንጀት መከላከያ ሰራዊቱን የሚያነቃቁ ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ቀርበዋል።

በሀገር ላይ የተከፈተውን ጦርነት ለመመከት ሁሉም በእልህና በአልደፈር ወኔ በተለያዩ ግንባሮች እየተሳተፈ ነው ያሉት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤው አገኝሁ ተሻገር፥ የኪነጥበብ ባለሙያዎችም ግንባር ድረስ በመገኘት የወገንን ጦር በማበረታታትና በማነቃቃት ከፍተኛ ድርሻ ወስደዋል ብለዋል።

አፈጉባኤው በተለያዩ ግንባሮች በመገኘት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሰራዎችን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በማቅረብ የማሸነፍ ወኔን ላቀዳጁና ድል እንዲመዘገብ ጥረት ላደረጉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፥ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኝው ሰራዊት የሚያነቃቃ የኪነ ጥበብ ዝግጅት መቅረቡ የሞራል ብርታት በመስጠት በግንባሩ ጠላትን እንድናሸነፍ ያስችለናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን በሙዚቃ ማነቃቃት ትንሹ የሙያ ግዴታችን ነው ያሉት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፥ የኢትዮጵያ ጠላቶች እስኪ ጠፉ ድረስ ሙያዊ አበርክቷችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት።

የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ካቀረቡ ድምፃውያን መካከል ድምጻዊ መስፍን በቀለ ፣ ደመረ ለገሰ እና  ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ይገኙበታል።

 

በምናለ አየነው

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.