Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ህወሓት ያወደማቸውን 10 የህክምና ተቋማት ግብዓቶች መልሶ ለማቋቋም ሙሉ ኃላፊነት ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባደረገው ጥሪ መሰረት በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በህወሓት የሽብር ቡድን ከወደሙት የህክምና ተቋማት ውስጥ 10 ጤና ጣቢያዎች መልሶ ለማቋቋም ኃላፊነት በመውሰድ ስራ መጀመሩን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ ገልጸዋል፡፡
የቢሮው ማኔጅመንት አባላት፣ የክልሉ የግል ጤና ተቋማትና የማህበረሰብ ተወካዮች የህክምና ግብዓቶችንና ሰብዓዊ ድጋፍ በመያዝ በጦርነት የተጎዱ የዞኑ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ተመልክተዋል፡፡
በምልከታቸውም የጉዳታቸውን መጠን ለመለየት ከሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ጋር የመረጃ ልውውጥ አድርገዋል፡፡
በዞኑ ከወደሙት ውስጥ 10ሩን የህክምና ጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ለማድረግ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የመጀመሪያ ዙር ሰብዓዊ ድጋፍና የህክምና ግብዓቶችን በመያዝ ወደ አንፆኪያ ገምዛና ኤፍራታና ግድም ወረዳዎች መምጣታቸውን ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ ተናግረዋል፡፡
የደረሰውን ውድመት በጋራ ልንካፈል የመጀመሪያ ዙር ድጋፋችንን ጀምረናል ያሉት ኃላፊዋ÷ በዚህም መሰረት 10ሩን ጤና ተቋማት ጉዳት ለይተን ከተመለስን በኋላ መሰረታዊ ድጋፍ የምናደርግ ይሆናል ብለዋል፡፡
ተቋማቱ ለማህበረሰቡ ሙሉ ለሙሉ የህክምና አገልግሎት መስጠት ደረጃ ላይ እስከሚደርሱ ድረስ የህክምና ግብዓት በማሟላት በኩል ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነት ወስደናልም ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋሹ ክንዱ÷ የሲዳማ ክልል የጤና ቢሮ የአማራ ክልል በወራሪው ኃይል ያደረሰውን ችግር ለመጋራት የወሰደው ኃላፊነት በዚህ ክፉ ቀን ከጎናችን በመቆም ሊሰሩ ያቀዱት በጎ ተግባር ወደፊት በታሪክ ተሰንዶ የሚቀመጥ አሻራ ነው ማለታቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.