Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓውን ቅኝ ገዢን ያሸነፈች ኢትዮጵያ ከውስጧ በተነሳ አሸባሪ አትፈርስም

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1896 ጣሊያንን አድዋ ላይ በተካሄደው ጦርነት ያሸነፈች እና በአውሮፓ ኃይሎች ቅኝ ያልተገዛች ሀገር በመሆኗ በሀገሪቷ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ትፈርሳለች ብሎ ማሰብ ታሪኳን ወደ ኋላ ሄዶ ካለማየት የመጣ መሆኑን ቤንጃሚን ኡጁማዱ ገለጸ፡፡

ቤንጃሚን ኡጁማዱ ዘ ጋርዲያን ላይ ባስነበበው ጽሁፍ፥ የኢጣሊያን በኢትዮጵያ መሸነፍ ሀገሪቷ ቀደም ብሎ በምስራቅ አፍሪካ ለመስፋፋት የነበራትን የቅኝ ግዛት ዕቅድ እና አዝማሚያ በእንጭጩ የቀጨ አጋጣሚን ፈጥሯልም ብሏል፡፡

አጋጣሚው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እንድትከበርና በአፍሪካውያን ደግሞ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆና እንደ መዲና እንድትቆጠር ያደረገ ነበርም ብሏል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ መሆኗ ሀገራቱ የውስጥ ችግሮቻቸውን የሚወያዩበትና ከኢትዮጵያም መፍትሄ የሚሹበትን ምኅዳር እንደፈጠረ፣ ለኢትዮጵያ ያላቸው መረዳትም ሀገሪቷ የራሷን ችግር ከመፍታት አልፋ ለአፍሪካውያኑ መፍትሄ የምትሻ ጠንካራ ሀገር እና ተምሳሌት ሆና እንደምትቆጠር ጸሃፊው አመላክቷል፡፡

የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም እንደ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ እና የተባበሩት መንግሥታት ያሉ አካላት በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው ግጭት አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ መንግስትን ጥቃት ፈጻሚ አድርገው ማቅረባቸው ግድያና በሀገሪቷ ውስጥ ውድመቱ እንዲባባስ ማድረጉን ጽሑፉ አመልክቷል፡፡

የምዕራባውያኑ አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በመደገፍ የፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ጭፍጨፋ ለመሸፈን መጣራቸው፣ ብሎም አውድ እና ታሪክ ያላገናዘበ የሃሰት ዘገባ ሲሰሩ መቆየታቸው ግጭቱ በአጭር ጊዜ መፍትሄ እንዳያገኝ ማድረጉን ጸሐፊው አመልክቷል፡፡

በአሜሪካ እና በአውሮፓ ኅብረት ዴሞክራሲ ቦታ የሚኖራት ከሀገራቱ ፖሊሲ ጋር የተሰናሰለ ከሆነች እንጂ አትታወቅም ብሏል ቤንጃሚን ኡጁማዱ፡፡

በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ነፍጎ ጫካ ከገባ አሸባሪ ቡድን ጋር ማበር ብሎም በቡድኑ የተጨፈጨፉትን ከ1ሺህ500 በላይ ንጹኃን በሚቆጣጠሯቸው መገናኛ ብዙኃን እንዳይዘገብ ማድረግ በሀገራቱ “ዴሞክራሲ” አንጻራዊ እንደሆነ ማሳያ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ይላል ጸሃፊው ምንም እንኳን የሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት ችግሮች እኩል ተመልክተን በራሳቸው እንዲፈቱ ሲያልፍም በአፍሪካ ሀገራት እንዲፈታ መደገፍ ቢያስፈልግም በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን ግልጽ አድልዖ ግን በተለየ ሁኔታ ተመልክተን ከምዕራባውኑ ሀገራት ፖለቲካዊ ፍላጎት እና ጫና ነጻ በሆነ መንገድ ችግሩ በእኛ በአፍሪካውን እንዲፈታ ልንሰራ ይገባል ብሏል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.