Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ወቅት ከሁሉም ቅድሚያ የምንሰጠው በሃገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም ነው- የጋምቤላ ህዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃገር የውስጥ ጉዳዮች የማንስማማባቸው ጉዳዮች ቢኖሩንም በዚህ ወቅት ከሁሉም ቅድሚያ የምንሰጠው በሃገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም ነው ሲል የጋምቤላ ህዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ገለጸ፡፡
 
ንቅናቄው ከዚህ ቀደም የህወሃት ሽብር ቡድኑ ሃገር በሚመራበት ወቅት የጋምቤላ ክልልን ሃብትና ንብረት ያለ አግባብ መዝረፉን በመቃወም ወደ ትጥቅ ትግል ገብቶ እንደነበር አስታውሷል፡፡
 
በተለይ በጋምቤላ ክልል በተፈጸመ የዘር ጭፍጨፋ የዚህን ቡድን አደገኛነት አስቀድሞ የተረዳው የክልሉ ህዝብ ለህልውናው ሲል አስቀድሞ ሲታገለው እንደነበር ነው የገለፀው።
 
በአሁኑ ሰዓትም ይህ ዘራፊ እና ገዳይ ሃይል ያለፈው በደል ሳያንሰው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የማያባራ ጦርነት መክፈቱ ንቅናቄው በጽኑ የሚታገለው መሆኑን ገልጿል፡፡
 
በምርጫ እና በሌሎች መሰል ጉዳዮች ንቅናቄው ያልተስማማቸው ጉዳዮች ቢኖሩትም ከሁሉም የሚቀድመው በሃገር ጉዳይ በጋራ መቆምና ሃገርን ከጥፋት ሃይል ማዳን ሊሆን ይገባልም ብሏል።
 
በመሆኑም የጋምቤላ ህዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ጋህ ሃገር በማዳን ትግሉ ከመንግስት ጋር በመቆም የዚህ ታሪካዊ የሃገር ጥሪ አካል እንደሚሆን ፖርቲው ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አረጋግጧል።
 
ጋህነዴን እስከ 2010 አመተ ምህረት በጋምቤላ እና በጎረቤት ሃገራት በመንቀሳቀስ አስከፊውን ስርዓት ሲታገል ቆይቶ በለውጡ መንግስት በተደረገ በሃገር ውስጥ እየተንቀሳቀሳ ያለ መሆኑም ተገልጿል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.