Fana: At a Speed of Life!

ኬሊያን ምባፔ በጥር ዝዉዉር መስኮት ፒ ኤስ ጅን እንደማይለቅ አስታወቀ

አዲስ አበባ ታህሳስ 20፣ 2014(ኤፍ ቢሲ) ፈረንሳዊዉ ኮከብ ኬሊያን ምባፔ በጥር ዝዉዉር መስኮት ፒ ኤስ ጅን እንደማይለቅ እና ከክለቡ ጋር ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማንሳት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡

ተጫዋቹ በጥር የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን ይቀላቀላል በሚል የሚወጡ መረጃዎችን አስመልክቶ በሰጠዉ ምላሽ፥ በጥር ወር ክለቡን የመልቀቅ እቅድ እንደሌለዉ እና ከክለቡ ጋር ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማንሳት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡

ከክለቡ ጋር ጠንክሬ እየሰራሁ ነው የቻምፒዬንስ ሊጉን ዋንጫን ለማሸነፍ የምችለውን ሁሉ እያደረኩኝ ነው፤ ተጨማሪ ዋንጫዎችን በማንሳት ደጋፊዎቼን ማሰደሰት እፈለጋለሁ ሲል መናገሩን ጎል ዶት ኮም ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ አዲስ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀዉ ኬሊያን ምባፔ ከሪያል ማድሪድ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡
ምባፔ በፒ ኤስ ጅ ቆይታዉ ባደረጋቸዉ 179 ጨዋታዎች 139 ጎሎችን ለክለቡ ማስቆጠር ችሏል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.