የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የአይነት ድጋፍ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

December 29, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ክልሉ ከዚህ ቀደም በርካታ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን፥ በዚህኛው ዙር ድጋፉም 11 ሺህ ሽርጦች፣ 500 ካርቶን ቴምር እና 150 ካርቶን ወተት ለሰራዊቱ ድጋፍ ማድረጉን ከብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡