Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አጽድቋል፡፡
 
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባ ነው የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅ 1265/2014 በ13 ተቃውሞ፣በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ያጸደቀው።
 
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ÷ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ የሆነው ይህ ኮሚሽን ሥራውን ገለልተኛ እና ተዓማኒ እንዲሁም አካታች በሆነ መልኩ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።
 
በሀገራዊ ጉዳዮች ሀገራዊ እና ተቀራራቢ አመለካከት ለመያዝ ከሚያበቁ ተቋማት አንዱ ይህ ኮሚሽን መሆኑንም አስገንዝበዋል።
 
የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ÷ ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር እይታ ከተመራበት ጊዜ አንስቶ የአዋጁን ክብደት ከግምት በማስገባት ይፋዊ የህዝብ ውይይት ሲደረግበት እንደቆየ ገልጸዋል።
 
በፍሬህይወት ሰፊው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.