Fana: At a Speed of Life!

የቀበሌ ንብረቶችን ቤታቸው ውስጥ በመደበቅ ከዘራፊው ቡድን የታደጉት ግለሰብ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወልዲያ ከተማ አንድ ግለሰብ የቀበሌያቸውን ንብረት በመደበቅ ከአሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ቡድን ዘረፋ እና ውድመት ታድገዋል፡፡
 
ወራሪው እና ዘራፊው አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል፡፡
 
ንጹሃን ዜጎችን ያለምንም ርህራሄ በጭካኔ ጨፍጭፏል፤ እናቶች እና ህጻናትንም ከሰብዓዊነት ባፈነገጠ መልኩ ቡድን ደፍሯል፡፡
 
አሸባሪው ቡድን በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች የሚፈጽማቸውን እኩይ ድርጊቶችን ለማክሸፍም በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን አስይዘው የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ከውድመት ከመታደግ ባለፈ ለወገን ጦርም ደጀንነታቸውን በተለያዩ መንገዶች አሳይተዋል፡፡
 
አቶ ልዑልሰገድ ወልዴም ከእነዚህ ጠንካራ እና ተቆርቋሪ ዜጎች ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡
 
አቶ ልዑልሰገድ ነዋሪነታቸው በወልዲያ ከተማ አየር ጤና አካባቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
 
ግለሰቡ ራስን ከወራሪው መከላከል ከባድ በሆነበት አስቸጋሪ ወቅት በተለይ የቀበሌው ንብረት የሆኑ ኮምፒዩተሮችን፣ የኮፒ እና የፕሪንት ማሽኖችን ኃላፊነት ወስደው በቤታቸው ደብቀው ከዘረፋና ውድመት ታድገዋል።
 
ከቁሳቁሶች በተጨማሪ የቀበሌውን ልዩ ልዩ ማህተሞች ደግሞ ባለቤታቸው በፔስታል በመጠቅለል በአትክልት ስፍራ ደብቀው ማትረፋቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ የሚመጣባቸውን ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተው መልካም ተግባሩን መፈጸማቸውን ነው አቶ ልዑልሰገድ የገለጹት፡፡
 
በለይኩን ዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.