Fana: At a Speed of Life!

ወደ አገር ቤት ለገቡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ይፋዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ አገር ቤት ለገቡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ይፋዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተከናወነ፡፡

በመርሃ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

መርሃ ግብሩን በንግግር በይፋ ያስጀመሩት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፥ የዳያስፖራ ማህበረሰቡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያልተገቡ ጣልቃ ገብነቶችን አጥብቆ ሲኮንን መቆየቱን አንስተው ፓን አፍሪካኒዝምን እና መላው ጥቁር ህዝቦችን ያነቃቃ እንቅስቃሴ ነው ብለዋል፡፡

ወራሪው ሃይል ኢትዮጵያን ለማዋራድ በርካታ አስነዋሪ ድርጊቶችን ፈጽሟል ያሉት አቶ ደመቀ፥ ትግሉ ገና መሆኑን አንስተዋል፡፡ በወራሪው ሃይል የቆየው ህዝብ የኛን ድጋፍ ይሻልም ነው ያሉት፡፡

የዲፕሎማሲ ትጥቆችን ታጥቃችሁ እንደምትመለሱም እናምናለን በማለት ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥ ወደ አገራቸው ለመጡ ዳያስፖራዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዚህም ዳያስፖራው የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት በመቃወም በቃ ሲሉ የተቃውሞ ድምፁን ማሰማቱን አንስተው ለዚህም አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባደረጉት ጥሪ ዳያስፖራው ወደ አገር ቤታቸው መምጣታቸውን ልዩ ታሪክ ነውም ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

በከተማዋ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ለ14 ቀን የሚቆይ ባዛር መከፈቱን ገልጸው፥ በኢትዮጵያ ምርት እንዲኮሩ እና አገራቸውን በተለያየ መስክ እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ ዶክተር መሃመድ እድሪስም በኢትዮጵያ የዳያስፖራውን ተሳትፎ ተጨባጭ እና የሚዳሰስ ሚና እንዲኖረው ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በመሰረት አወቀና ቆንጂት ዘውዴ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.