Fana: At a Speed of Life!

ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አልተሰበሰበም – የገቢዎች ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ታህሳስ 20፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሊሰበሰብ እንዳልቻለ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 በጀት ዓመት 360 ቢሊየን ብር የመሰብሰብ እቅድን አስቀምጦ ሥራ የጀመረ ሲሆን፥ ባሳለፍናቸው አምስት የበጀት ዓመቱ ወራት 158 ነጥብ 9 ቢሊየን ለመሰብሰብ አቅዶ 147 ነጥብ 3 ቢሊየን ወይንም የእቅዱን 92 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡
 
በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል የገቢ አፈጻጸሙን አስመልክቶ እንደገለጹት፥ ሀገራችን በተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ እና የኮቪድ ወረርሽኝ ችግር ውስጥ ሆነን የተመዘገበ እንደመሆኑ የገቢ አፈጻጸሙ ስኬታማ ነው ሊባል ይችላል ብለዋል፡፡
 
ለዚህም ግብር ከፋዮች፣ የግብር ሰብሰባቢው ተቋም ሰራተኞችን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡
 
በአመስቱ ወራት በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በመቀሌ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች በድምሩ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ቢታቀድም ምንም ገቢ ያልተሰበሰበ መሆኑን እንዲሁም በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ብቻ ለመሰብሰብ እንደተቻለ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
 
በዚህም ከመቀሌ እና ኮምቦልቻ አራት ቅርንጫፎች ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ውስጥ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ብቻ ሲሰበሰብ ቀሪው 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ሳይሰበሰብ መቅረቱን ዳይሬክተሯ ጨምረው መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.