የሀገር ውስጥ ዜና

በህወሃት የሽብር ቡድን የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት በመረባረብ ሊፈጠር የሚችልን ስራ አጥነት ማስቀረት ይግባል – አቶ ንጉሱ ጥላሁን

By Alemayehu Geremew

December 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በተሻሻለው የኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ላይ ሥልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ሥራ አጥነት ኢኮኖሚያዊ ፣ ማኅበራዊ እና በዜጎች ላይ ሥነ-ልቦናዊ ጫና የሚያስከትል በመሆኑ ችግሩን ለማቃለል የመርሃ ግብሩ ሰልጣኞች ስትራቴጂ፣ ደንብ ፣ መመሪያ እና ሌሎችንም የድጋፍ ማዕቀፎች መሠረት አድርገው በመስራት የሚሊየኖችን ጥያቄ መመለስ እንዲቻል ትልቅ ኃላፊነት ወስደው ሊሰሩ እንደሚገባ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

በአማራ እና በአፋር ክልሎች በኢንተርፕራይዞች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አቶ ንጉሱ ጠቁመዋል።

እነዚህን አካባቢዎች በርብርብ መልሶ መገንባት ወይም መጠገን ካልተቻለ በክልሎቹ ሥራ አጥነት እንደሚጨምርና የኢኮኖሚው ትልቅ ህመም ሆኖ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከሥራ ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!