Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከ37ሺህ ቶን በላይ እህል አወደመ

አዲስ አበባ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ በደረሰ ከባድ የጎርፍ አደጋ 37 ሺህ 624 ቶን የሚገመት እህል መውደሙን ዓለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አስታውቋል፡፡
 
ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ 65 ሺህ 107 ሄክታር መሬት በውሃ መጥለቅለቁንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡
 
ፋኦ 65 ሺህ107 ሄክታር የሚጠጋ መሬት በጎርፍ መጎዳቱን እና 37 ሺህ 624 ቶን እህል በጎርፉ እንደተወሰደ ባደረኩት የመጀመሪያ ጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል።
 
ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ዋስትና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው አናዱሉ ድርጅቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ የጎርፍ አደጋው ለአመታት በመደጋገሙ ምክንያት ተቋቁመው በህይወት ለመኖር አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡
 
በሀገሪቱ ከሚገኙ 10 ግዛቶች በስምንቱ አደጋው መከሰቱ የተገለጸ ሲሆን ከ835 ሺህ በላይ ሰዎች ተጎድተዋል፤ በተለይ ጆንግሌይ፣ ዩኒቲ እና የላይኛው ናይል በከፋ አደጋ የተጎዱ ቦታዎች መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል።
 
በዚህ የጎርፍ አደጋ 795 ሺህ 558 የቤት እንስሳት መሞታቸውንም ዘገባው ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.