Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ በድንበር አካባቢዎች የኮሮና እና ሌሎች ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚውል 60 ሚሊየን ዩሮ መደበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድንበር አካባቢዎች የኮሮና ቫይረስ እና ሌሎች ወረርሽኞችን ለመከላከል 60 ሚሊየን ዩሮ መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አስታወቀ።
 
ድርጅቱ ኮሮናን ጨምሮ ድንበር ዘለል የወረርሽኝ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጎንደር ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
 
በኢጋድ የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና አስተባባሪ ዶክተር ግሩም ሃይሉ በወቅቱ እንደገለጹት÷ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ለመከላከል ለሚከናወኑ ሥራዎች የተመደበው ገንዘብ ከአውሮፓ ሕብረት የተገኘ ድጋፍ ነው።
 
ገንዘቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ የድርጅቱ አባል ሀገራት የኮሮና ቫይረስና ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቅንጅታዊ አሰራርን እንዲያዳብሩ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
 
አባል ሀገራቱ በድንበር አካባቢ ኮሮናን በመከላከልና በመቆጣጠር 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ህዝብ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረጉ መሆኑንም ዶክተር ግሩም አመላክተዋል፡፡
 
በኢትዮጵያም በአፋር፣ በሞያሌና በመተማ አካባቢዎች ከአጎራባች ሀገራት ጋር በሚካሄድ የንግድ እንቅስቃሴ የኮሮና ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ከአቅም ግንባታ በተጨማሪ የመከላከያ ግብአቶች ድጋፍ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡
 
የምክክር መድረኩ ዓላማም አባል ሀገራት በድንበር አካባቢ ጠንካራ የመረጃ ልውውጥና የመደጋገፍ ባህል በማሳደግ ለወረርሽኙ የሚሰጡትን ምላሽ ማጠናከር መሆኑንም ዶክተር ግሩም ገልጸዋል።
 
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በማድረግ፣ እጆችን በመታጠብና አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ይሰራል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ለሁለት ቀናት በቆየው የምክክር መድረክ ላይ የጤና ባለሙያዎችና የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.