Fana: At a Speed of Life!

በ194 ሰዎች ሞት ወንጀል በተከሰሱ ግለሰቦች የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሶሳ እና አካባቢው አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ካማሽ ወረዳ በ194 ሰዎች ሞት እና 27 ሚሊየን ብር በሚገመት ንብረት ውድመት ወንጀል ከተከሰሱ 21 ሰዎች መካከል በአስሩ ላይ የጥፋኝት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
 
ችሎቱ የጥፋተኝነት ውሳኔውን ያሳለፈው በእነ ጸጋዬ ተሰማ የክስ መዝገብ ክስ በቀረበባቸው ላይ ነው፡፡
 
በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጸው፥ በካማሽ ወረዳ ከመስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወር 2011 ዓ.ም. ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡
 
በግጭቱ የ194 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች ከአካባቢው መፈናቀላቸውንና በግጭቱ 27 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታውቋል፡፡
 
ወንጀሉ የተፈጸመው በጦር መሳሪያ እና በስለታም መሳሪያዎች ጭምር እንደሆነ አመላክቷል፡፡
 
ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ በእነጸጋዬ ተሰማ የክስ መዝገብ በ21 ሰዎች ላይ የእርሰ በርስ ጦርነት በማስነሳት፣ በመሳተፍ እና በከባድ የግድያ ወንጀል ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡
 
የቀረበባቸውን ክስ በማረሚያ ቤት ሆነው በጊዜ ቀጠሮ ሲከታተሉ ከነበሩ 21 ተከሳሾች መካከል የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ በአስሩ ላይ ከ30 በላይ የሰው ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጃ ማቅረቡ ተመላክቷል፡፡
 
አስሩ ግለሰቦች በክስ መዝገቡ የቀረበባቸውን ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሶሳ እና አካባቢው አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ዛሬ በአሶሳ ከተማ በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስተላለፉን የጠቅላይ አዐቃቤ ህግ ዘርፍ አስታውቋል።
 
ቀሪ 11 ተከሳሾች ደግሞ የዐቃቤ ህግ የሰው ምስክሮች ባለመቅረባቸው ምክንያት ከክሱ ነጻ የወጡ እና ክሳቸው ለጊዜው የተቋረጠባቸው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
 
ጥፋተኛ የተባሉ ተከሳሾች ወንጀሉን የፈጸሙት ጉዳያቸው በሌላ የወንጀል ክስ መዝገብ እየታየ ከሚገኝ ሌሎች 210 ሰዎች ጋር በመተባበር እንደሆነም ነው የተመለከተው።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.