Fana: At a Speed of Life!

የሀኪም ግዛው መታሰቢያ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከ16 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተበረከተለት

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ስር ለተገነባው የሀኪም ግዛው ማስተማሪያ ሆስፒታል ከ16 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ሂዉማን ብሪጅ ከተሰኘ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተበረከተለት፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የሂውማን ብሪጅ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶክተር አዳሙ አንለይ ፥ ማስተማሪያ ሆስፒታሉን ስራ ለማስጀመር በገባነው ቃል መሰረት ለታካሚ ምቹ የሆኑ ዲጂታላይዝድ አልጋዎችና ዊልቸሮችን በድጋፍ አስረክበናል ብለዋል፡፡
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ቴዎድሮስ ክፍለ ዮሃንስበድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት ፥የትህነግ ሽብር ቡድን በምስራቅ አማራ በህክምና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድምት ባደረሰበት ማግስት ካንትሪ ብሪጅ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለሆስፒታላችን ያደረገው ድጋፍ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሸፈንና ስራችንን በቶሎ ለመጀመር ያስችለናል ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ ካንትሪ ብሪጅ ግብረ ሰናይ ድርጅት የማስተማሪያ ሆስፒታሉን ስንገነባ ጀምሮ ከጎናችን ነበር ብለዋል።
ድርጅቱ የገባውን ቃል ጠብቆ እጅግ ዘመናዊና ዲጂታል የሆኑ አልጋዎችን ከነፍራሻቸው፣ ዊልቸሮችና የድጋፍ መንቀሳቀሻ መሳሪያዎችን በመደገፍ ላሳየው አጋርነት አመስግነዋል፡፡
የዲጂታል አልጋው ዋጋ ከነፍራሽ 120 ሺህ ብር እንደሆነ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ተገልጿል።
ድርጅቱ 138 ያህል አልጋዎችን እንዲሁም 15 ዊልቸርና የድጋፍ መንቀሳቀሻ መሳሪያዎችን ለሆስፒታሉ አበርክቷል፡፡
የሀኪም ግዛው መታሰቢያ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ስራ ለማስጀመር የሚያስችሉ የባለሙያና የህክምና ግብዓቶችን የማሟላት ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑንም የስራ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡
በግርማ ነሲቡ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.