Fana: At a Speed of Life!

የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ስርዓት ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ስርዓትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ይህ ስርዓት ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አዲስ ፍቃድ ማውጣት ፣ ዓመታዊ ፍቃድ ማደስ ፣ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ማስመዝገብ ፣ የጉዞ መርሃ ግብርን ማሳወቅ ፣ የድንበር ተሻጋሪ መታወቂያዎችን መስጠት እና የተሽከርካሪዎችን የጉዞ እርቀትና ጭነትም ማሳወቅ የሚያስችል ነው።
በመርሀ ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር የሹመት ግዛውናየተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ወጪ እና ገቢ ጭነቶችን በማጓጓዝ ሂደት የተሽከርካሪዎች ድርሻ ከ90 በመቶ በላይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ደግሞ ቀሪውን ድርሻ እንደሚወስድ ተናግረዋል፡፡
በአሁን ሰዓትም 98 የድንበር ተሸጋሪ የንግድ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ኦፕሬተሮች እንዲሁም ከ12 ሺህ 700 በላይ የንግድ ጭነት ተሸከርካሪዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበርና በድርጅት ዘርፍ ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
3ሺህ 500 የሚጠጉ የፍሳሽ ማመላለሻ የንግድ የጭነት ተሸከርካሪዎችም ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡
ይህም የሃገሪቱ የመንገድ ትራንስፖርት ዘርፍ ወጪና ገቢ ንግድ ስርዓት የጀርባ አጥንት በመሆን የጎላ ድርሻ እያበረከቱ መሆኑን ያመላክታል ብለዋል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የወጪ ንግድ የተቀላጠፈ ለማድረግም የሎጀስቲክስ አገልግሎቱን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ለዚህም ይፋ የተደረገው የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ስርዓት ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብለዋል።
በዘመን በየነ እና በፌቨን ቢሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.