የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

December 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ማለትም ከግጭት በኋላ ስለሚደረገው መልሶ ግንባታ እና ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

ሁለቱም ወገኖች ሀገራቱ በቀጣይ ሊሰሩባቸው የሚችሉ የትብብር ዘርፎችን መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!