Fana: At a Speed of Life!

ክልሎች የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያደርጉት ድጋፍ ኢትዮጵያዊነት ያመጣው ስሜት ነው – ዶክተር ከይረዲን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎችና ተቋማት የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያደርጉት ድጋፍ ቁስ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ስሜት ያመጣው አንድነት ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንትሮፖሎጂስትና የብዝሀነት ተመራማሪ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ ገለጹ፡፡

አሸባሪው ህወሓት ከቁስ በዘለለ በኢትዮጵያ የአብሮነት እሴት ላይ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በስነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጉዳት ማድረሱን እና አደጋው ጥልቀት ያለው መሆኑን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

በገዳማትና በመስጂዶች ያሉ ወገኖች ችግር ሲገጥማቸው እንደነበር የገለጹት ዶክተር ከይረዲን÷ እነዚያ ቦታዎች በዓለም የግጭት ታሪክ ውስጥ የትኛውም የግጭት ተዋናይ የሚጠለልባቸው ቦታዎች መሆናቸውን አውስተዋል።

˝ኢትዮጵያውያን የተሳሰርን ነን፣ ጉዳቱ ሁሉንም ነው የነካው፣ ለረጅም ዘመናት ከገነባነው የአብሮነት እሴት አንጻር ኢትዮጵያውያን ከባድ መጥፎ መንፈስ ውስጥ እንድናልፍ ያደረገ ግጭት ነው ̋ ብለዋል፡፡

በዚህ ግጭት የተዳከመው የኢትዮጵያውያን የአብሮነት እሴት ተነስቷል ያሉት ዶክተር ከይረዲን÷ በሁሉም እምነት ያሉ የሃይማኖች መሪዎች ሲናገሩ አንድ ናቸው፣ በማህበራዊ ህይወት ላይም ተመሳሳይ እሴት አለን ሲሉም አስረድተዋል።

ክልሎች ከየአቅጣጫው ያላቸውን ድጋፍ ሰብስበው የወደሙትን ተቋማት ለመገንባት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሆኑን እና ጦርነቱን ለመመከት የመጣውን አንድነት እንደ በረከት መውሰድ እንደሚቻል አንስተዋል፡፡

የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው÷ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ባለው ርብርብ ኮርተናል፣ አንዳንድ ተቋማትን በፍጥነት መልሶ መገንባት ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

ስናነብና ስንሰማ የነበርነውን ታሪክ ይሄ ትውልድ የሀገር ተጋድሎን በአይናችን እንድናይ አድርጎናልም ብለዋል፡፡

በክፉ ሰዓት ማንም እንደማይደርስል ያነሱት ዶክተር ከይረዲን፥ የውጭ ሃይሎች ሲነኩን አንድ ሆነን እንደተነሳነው ሁሉ በውስጥ ጉዳያችንም በአንድነት መነሳት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.